ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ሽልማት

ከህዳር 6-14 የተካሄደው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በትላንትናዉ እለት መዝጊያ እና የሽልማት ፕሮግራሙን አካሂዷል። በእለቱ በርካታ የኪነጥበቡ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የሽልማቱን ትኩረት ደግሞ ዶሎቪ ወስዷል።

ዜና ክፍል · · 2 ደቂቃ ንባብ · 1

ዶሎቪያ ፊልም በአመቱ ምርጥ ሲኒማቶግራፊ፣ በአመቱ ምርጥ ዳይሬክቲንግ እንዲሁም የአመቱ ምርጥ ፊልም ሽልማትን በመዉሰድ የምሽቱ ድምቀት ሆኗል። ሽልማቱንም የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር በሃይሉ እንግዳ ተረክቧል። መቀነት ፊልም የአመቱ የዳኞች ምርጫን አሸንፏል።

በትወናው ዘርፍ በታሪክ ለሶስተኛ ጊዜ ምርጥ ተዋናይ ለመባል ያበቃዉን የአመቱ ምርጥ ወንድ ተዋናይ ዘርፍ ያሸነፈው ሳምሶን ታደሰ በሁለት ፊት ፊልም ሲሆን ካሁን በፊት በመጀመሪያው እና ሶስተኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ አሸንፏል።

አንጋፋዋ ተዋናይት ፍቅርተ ደሳለኝ በሹም ሽረት ፊልም በሴት መሪ ተዋናይነት አሸንፋለች።
በረዳት ተዋንያን ዘርፍ ንጉስ ባይሌ ከአንተነህ ፊልም እንዲሁም ሃና ግደይ ከዲያስፋራው ፊልም አሸንፈዋል። የአሸናፊዎቹ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

👉ምርጥ ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ አሸናፊ
ዮሴፍ ባዘዘው፣ ከመቀነት ፊልም

👉ምርጥ ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት
ህጻን ማርያማዊት ሰለሞን፣ ከጀሚላ ፊልም

👉ምርጥ አጭር ፊልም
የመጨረሻው እራት ፊልም

👉ምርጥ የሞባይል ፊልም
ነጻነት ፊልም

👉ምርጥ ልዩ ዶክመንታሪ (ዘጋቢ ፊልም)
Inspired by Deborah (ኢንስፓየርድ ባይ ዲቦራ)

👉ምርጥ ረዳት ወንድ ተዋናይ
ንጉስ ባይሌ፣ ከአንተነህ ፊልም

👉ምርጥ ረዳት ሴት ተዋናይት
ሀና ግደይ፣ ከዲያስፋራው ፊልም

👉ምርጥ ወንድ ተዋናይ
ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ)፣ ከሁለት ፊት ፊልም

👉ምርጥ ሴት ተዋናይት
ፍቅርተ ደሳለኝ፣ ከሹምሽር ፊልም

👉ምርጥ የዳኞች ምርጫ
መቀነት ፊልም

👉ምርጥ የፊልም ጽሁፍ
ሳምሶን ታደሰ ጓንጉል፣ ከሁለት ፊት ፊልም

👉ምርጥ ሲኒማቶግራፊ
ኤልያስ ተስፋዬ፣ ከዶሎቪያ ፊልም

👉ምርጥ ዳይሬክተር
በሀይሉ እንግዳ፣ ከዶሎቪያ ፊልም

👉የአመቱ ምርጥ ፊልም
ዶሎቪያ ፊልም

21ኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በቀጣዩ አመትም በአዳዲስ ዘርፎች እና በስፋት እንደሚመለስ የፌስቲቫሉ ዳይሬክተር ይርጋሸዋ ተሾመ ተናግረዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN