መቻል በፕሪሚየር ሊጉ የሚጠቀመው አዲስ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን በስድስት ጨዋታዎች 11 ነጥቦችን በመያዝ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ መቻል ዓለም የሚጠይቀውን የተጫዋቾችን አካላዊ ብቃት በጨዋታ እና በልምምድ ወቅት ለመተግበር የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ መጠወም ሊጀመር መሆኑን አሳውቋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ስታት ስፖርትስ ጂፒኤስ ቬትስ የተባለውን አዲስ ቴክኖሎጂን በሊጉ ከሰባተኛው ሳምንት ጀምሮ መጠቀም ሊጀምር መሆኑን ሀገሬ ቴሌቪዥን ከክለቡ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጥያቄ አቅራቢነት ወደ ሰባ ለሚደርሱ የቡድኑ አባላት ከሀገር ውጪ ተገዝቶ የመጣው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተጫዋቾቹን አካላዊ ብቃትን በመለካት የአሰልጣኞችን ስራ በአግባቡ የሚያቀለም ነው።
ቴክኖሎጂው ተጨዋቾች ከመለያቸው በውስጠኛው ክፍል በመልበስ በተጨማሪም በጨዋታ ወቅት አንድ ተጫዋች ሚሸፍነውን የሜዳ ርቀቱን ፍጥነቱን ፣ በእንቅስቃሴ ወቅት ደግሞ ያለበትን ጫና እና እየሸፈነ ያለውን የሜዳ ክፍል በግልፅ በቁጥር እና ምስል በዝርዝር የሚያሳውቅ የቡድኑ ተጨዋቾች በልምምድ ወቅት መጠቀም ጀምረዋል።
በክለብ ደረጃ መቻል ቀዳሚው ቢሆንም ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በያዙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም የዛሬ አመት በሞሮኮ በተደረገው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ላይ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ይህንን ቴክኖሎጂ መጠቀሙ ይታወሳል።
