ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ለተወዳጇ ጉማሬ ፊዮናን ልዩ መርሀ ግብር ሊደረግ ነው

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ክለብ ኤፍሲ ሲንሲናቲ በከተማዋ መካነ አራዊት በቅርቡ ህይወቷ ያለፈውን ተወዳጅ ጉማሬ ፊዮናን በቅዳሜው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በልዩ መርሃ ግብር ለማክበር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

እ.ኤ.አ. በ2017 ያለጊዜዋ ተወልዳ በማህበራዊ ሚዲያዎች ታዋቂነትን ያተረፈችው እና የሲንሲናቲ ከተማ መለያ የነበረችው የዘጠኝ ዓመቷ ጉማሬ ፊዮና፤ ባለፈው ሐሙስ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

ሲንሲናቲ በመጪው ቅዳሜ በኤም.ኤል.ኤስ ካፕ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናሽቪል ኤስሲን ሲገጥም የክለቡ ደጋፊዎች ቡድን ፊዮናን የሚያሳይ ግዙፍ የአቀባበል ምስል የሚያቀርብ ሲሆን ክለቡም ለእያንዳንዱ በስታዲየም ለሚገኝ ደጋፊ ለሲንሲናቲ መካነ አራዊት እና የእጽዋት መናፈሻ የገንዘብ ልገሳ ያደርጋል።

ፊዮና ባለፈችበት ቀን በተደረገው ጨዋታ ሲንሲናቲ ኦርላንዶን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ግብ ያስቆጠረው ተከላካዩ ኒክ ሃግሉንድ ደስታውን ለፊዮና መግለጹ የሚታወስ ሲሆን የሲንሲናቲ ቤንጋልስ አሜሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ቲ ሂጊንስም ለክብሯ የተዘጋጀ ማሊያ ለብሶ ታይቷል። ናሽቪል በኮንፈረንስ አንደኛ ሆኖ ቢያጠናቅቅም፣ ሲንሲናቲ የመጀመሪያውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፉ ቅዳሜ ድል ካደረገ ወደ ቀጣይ ዙር ያልፋል።

አጋራ

YouTube

አማEN