ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የዓለም አትሌቲክስ “አልቲሜት ሻምፒዮና” ከፍተኛ ዕይታ እና ለአዘጋጇ ሀንጋሪ 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ ይፉ ሆነ

ከመስከረም 1 እስከ 3/2019 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት የተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ “አልቲሜት ሻምፒዮና” በመም ላይ ካሳየው ፉክክር ባለፈ፣ በቴሌቪዥን ዕይታ እና በኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖው አስደናቂ ስኬት ማስመዝገቡን ዛሬ የአለም አትሌቲክስ ይፉ ያደረገዉ ሪፖርት አረጋግጧል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 3

የዓለም ሻምፒዮናዎችን፣ የኦሎምፒክ አሸናፊዎችን፣ የዳይመንድ ሊግ ባለድሎችን እና የዓመቱን ምርጥ አትሌቶች በአንድ መድረክ ያገናኘው ይህ ውድድር በቀጥታም ሆነ በድጋሚ ስርጭት 192 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል።

ይህም ገና በመጀመሪያ ዝግጅቱ ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመቀጠል በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ተመልካች ያገኘ ውድድር አድርጎታል።

በኒልሰን (Nielsen) የጥናት ሪፖርት መሠረት ውድድሩ በአጠቃላይ ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ጠቀሜታ ያስገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 83.6 ሚሊዮን ዶላሩ በቀጥታ ለቡዳፔስት ከተማ የተገኘ ገቢ ሆኗል፡፡

ይፉ እንደሆነዉ ሪፖርት ከሆነ የተመልካቾች እርካታ 98 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ከ90% በላይ የሚሆኑ የውጭ ሀገር ተመልካቾች ወደ ቡዳፔስት ተመልሰው የመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ 61,671 ትኬቶች በተሸጡበት መድረክ 15 የሀንጋሪ “ኦል-ካመርስ” (all-comers) ክብረወሰኖች፣ 4 የዓመቱ የዓለም ፈጣን ሰዓቶች እና 6 ብሔራዊ ክብረወሰኖች ተሰብረዋል።

የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ፤ “አልቲሜት ሻምፒዮና ለቴሌቪዥን ስርጭት ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ እና የአትሌቲክስ የውድድር ዘመንን በታላቅ ድምቀት የሚዘጋ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሀንጋሪ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቦር ፖስፋይ በበኩላቸው፤ “አዲስ ታሪክ የሰራዉ ዉድድር አካል በመሆናችን እና ከመላው ዓለም የመጡ አትሌቶችና ደጋፊዎች በሀንጋሪ መልካም ቆይታ በማድረጋቸው ኩራት ይሰማናል” ሲሉ ገልጸዋል።

በዉድድሩ ላይ ኢትዮጵያዉያኑ ልቅና አምባዉ በ5000ሜ ስታሸንፍ፣ ፉንታዬ በላይነህ 3ኛ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ 4ኛ፣ ቢኒያም መሀሪ 4ኛ ሆነዉ መጨረሳቸዉ ይታወሳል።

አጋራ

YouTube

አማEN