ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የክለብ ብሩዥ ደጋፊዎች ለምን “You’ll Never Walk Alone” ሲዘምሩ አመሹ?

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከ1978 የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት የቤልጂየሙ ክለብ ብሩዥ እና የእንግሊዙ ሊቨርፑል ደጋፊዎች፣ ከጨዋታው መጀመር በፊት በአንድ መዝሙር ታጅበው ድንቅ የእግር ኳስ ስፖርታዊ ጨዋታነት ሲያሳዩ አምሽተዋል፡፡

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከ1978 የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት የቤልጂየሙ ክለብ ብሩዥ እና የእንግሊዙ ሊቨርፑል ደጋፊዎች፣ ከጨዋታው መጀመር በፊት በአንድ መዝሙር ታጅበው ድንቅ የእግር ኳስ ስፖርታዊ ጨዋታነት ሲያሳዩ አምሽተዋል፡፡

በ1960ዎቹ በጀሪ ኤንድ ዘ ፔስሜከርስ ታዋቂነትን ያተረፈው እና ለአስርት ዓመታት የሊቨርፑል መለያ ሆኖ የቆየው “You’ll Never Walk Alone” መዝሙር፣ በቤልጂየም ጃን ብሬይደል ስታዲየም በሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች በጋራ ተዘምሯል።

እ.ኤ.አ. በ1978 በዌምብሌይ የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ እና ከዚያ ቀደም ብሎ በዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ተገናኝተው የነበሩት ሁለቱ ክለቦች፤ ከረጅም ዓመታት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ ክለብ ብሩዥ በመጀመሪያ በአንድ የክለቡ ደጋፊ በቀጥታ እንዲዘመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከተለያዩ ወገኖች በተሰጠ አስተያየት መሰረት ባህሉን በመጠበቅ በሁለቱም ደጋፊዎች በጋራ እንዲመራ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የስታዲየሙ አራቱም መቀመጫዎች ተነስተው የድምጽ ማጉያውን በመጠቀም መዝሙሩን በአንድነት በማሰማት፣ እግር ኳስ ከውድድር ባለፈ የአንድነት፣ የመከባበር እና የባህል መድረክ መሆኑን ያሳየ ታሪካዊ ትዕይንት አስመልክተዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN