የማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የመጀመሪያ ሳምንት!
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በመጀመሪያው ሳምንት የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታቸው ድል ማስመዘግብ ባይችሉም በተጨዋቾቻቸው እጅጉን መኩራታቸውን ተናግረዋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ትናንት ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ጨዋታቸውን 2 ለ 2 በሆነ የአቻ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ አሠልጣኙ በጨዋታው ከነበረው ዳኝነት ይልቅ የተጨዋቾቻው እንቅስቃሴ ላይ ማተኮርን መርጠዋል።
ከቀናት በፊት በተካሄደው የላንክሻየር ደርቢ የቀይ ካርድ ሠለባ የነበረውን ሌኒ ዮሮን ተከትሎ ዳኞች ላይ ትችታቸውን የሰነዘሩት ፖቼቲኖ ትናንት ግን ምናልባትም ቀያይ ሰይጣኖቹ ከሜዳቸው ውጪ የዓመቱን የመጀመሪያ ድል እንዳያስመዘግቡ እንቅፋት ከሆነባቸው የዳኝነት ስህተቶች በኋላ ዳኛውን ከመውቀስ ተቆጥበዋል።
አሠልጣኙ ተጨዋቾቻቸው ሀሳባቸውን ለመቀበል ያላቸውን ፍላጎት እና ዝግጁነት ሲያደንቁ የምሽቱ ጨዋታም የአሠልጣኙን ሀሳብ ተጨዋቾቹ መቀበል ስለመጀመራቸው ጥቂት ማሳያ ነበር።
ከፖቼቲኖ መምጣት በኋላ እስካሁን በካሪንግተን የሚደረጉት ልምምዶች ተጫዋቾቹን ከአዳዲስ ሃሳቦች ጋር ለማላመድ ካለ ሩጫ ጋር ከእስካሁኖቹ ሁሉ ረጅም እና ታክቲካዊ እየሆኑ መጥተዋል።
ፖቼቲኖ በመጀመሪያው ሳምንት ቆይታቸው ትናንት ምሽት ላደረጉት ሁለተኛው ጨዋታ ልክ እንደ ሊቨርፑሉ ጨዋታ ሁሉ በአራት ተከላካዮች ሲጀምሩ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝን አሁንም የግራ መስመር ተከላካይ አድርጎ መጫወትን መርጠዋል።
አልፎ አልፎ ከሚታዩ ስህተቶች ውጭ የስፖርቲንግ ሊዝበንን የማጥቃት እንቅስቃሴ በአብዛኛው የገታ የተከላካይ መዋቅር ነበራቸው።
ተከላካዮቹ ወደ ላይኛው ሜዳ ተጠግተው ተጫውተዋል ፣ ተጋጣሚ ብዙ ክፍት ቦታ እንዳያገኝ በተቀራራቢ መስመር ላይ ይገኙ ነበር እንዲሁም አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ በላይኛው ሜዳ ፕሬስ ለማድረግ ሲሞክሩ ተስተውለዋል።
ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ፖቼቲኖ በአምስት የልምምድ ክፍለ ጊዜያት ያስተላለፉት መልእክት በተወሰነ መልኩ መሳካቱን የሚያሳዩ ምልክቶች በመታየታቸው እርካታቸውን ገልፀዋል።
