ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ሁለተኛው የአፍሪካ ፊልም ገበያና ሽልማት መድረክ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማጠናከር፣ የፊልም ባለሙያዎችን ለማገናኘትና አህጉራዊ የገበያ ትስስርን ለማሳደግ ያለመው ሁለተኛው የአፍሪካ ፊልም ገበያና ሽልማት መድረክ (AAFMA 2026) በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና በኢትዮ-አርክዉድ ኢንተርቴይመንት በጋራ የተዘጋጀው ይህ መድረክ ከኅዳር 18 እና19 ቀን 2019 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንደገለጹት፣ መድረኩ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፊልም ፕሮዳክሽንና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እንዲሁም አፍሪካውያን በራሳቸው አንደበት ታሪካቸውን እንዲተርኩ ለማስቻል ያለመ ነው።

“የአፍሪካ ኦዲዮቪዥዋል ኢንዱስትሪ ስርዓትን መገንባት፡ ከእቅድ ወደ ተግባር” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ መድረክ ከ500 በላይ የአፍሪካ የፊልምና የሚዲያ ዘርፍ ባለሙያዎችን ያሳትፋል።

በመድረኩም በፖሊሲ፣ በሴቶች ተሳትፎ፣ በፊልም ትምህርትና በገበያ ትስስር ዙሪያ አራት የፓናል ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን አስቀድሞ በብሪቲሽ ካውንስል ድጋፍ የፊልም ኮስትዩም ዲዛይን ሥልጠም ተሰጥቷል፡፡

የፊልም ባለሙያዎች፣ ፕሮዲዩሰሮችና ሌሎች የጥበብ ዘርፍ ተዋናዮች በመድረኩ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

አጋራ

YouTube

አማEN