ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ማንችስተር ዩናይትድ ከሊጉ በወረደ ጊዜ!

ማንችስተር ዩናይትድ አዲሱን የውድድር ዘመን በ 40 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መጥፎ ውጤት ከጀመረ በኋላ የአሠልጣኝ ለውጥ አድርጓል።

ዜና ክፍል · · 2 ደቂቃ ንባብ · 2

ቀያይ ሰይጣኖቹ አሁን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያሉበት ደረጃ ለመጨረሻ ጊዜ ከሊጉ ከወረዱበት 1974 የውድድር ዘመን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ታሪክ ይጠቁማል።

በ 1968 ማንችስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ እግርኳስ ታሪክ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማሳካት ከቻለ በኋላ ታላቁ አሠልጣኝ ሰር ማት በዝቢ ራሳቸውን ከአሠልጣኝነት አገለሉ።

በቀጣዮቹ ስድስት አመታት ማንችስተር ዩናይትድ ዊልፍ ማክጊነስ ፣ ፍራንክ ኦፋሬል እና ቶሚ ዶከርቲን በአሠልጣኝነት ሲቀጥር ክለቡ ከመውረድ ስጋት ለመታደግ ደግሞ ሰር ማት በዝቢ በድጋሚ ተመልሰው የአሠልጣኝነቱን ስፍራ ይዘው ያውቃሉ።

ልክ እንደ ሰር ማት በዝቢ ጊዜ ሁሉ ማንችስተር ዩናይትድ ከሌላኛው ታላቅ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ በአጠቃላይ የ 12 አሠልጣኞች ለውጥ አድርጓል።

የኦልድትራፎርዱ ክለብ ባለፉት ስምንት አመታት ብቻ ጆዜ ሞሪኒሆ ፣ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ፣ ኤሪክ ቴን ሃግ ፣ ሩብን አሞሪም እና ማይክል ካሪክን ከስራቸው አሰናብቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ በ 1972 በክሪስታል ፓላስ 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ከተሸነፈ በኋላ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ የነበሩትን ቶሚ ዶከርቲን ነበር የሾመው።

ዶከርቲ ክለቡን በመጡበት ዓመት በሊጉ ቢያቆዩትም በቀጣዩ አመት ማንችስተር ዩናይትድ 21ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ለመጨረሻ ጊዜ ከሊጉ ለመውረድ ተገደደ።

አሁን ማንችስተር ዩናይትድ ልክ ሰር ማት በዝቢ ከለቀቁ በኋላ የነበረውን አስቸጋሪ ጊዜ ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላም እየደገመው ይገኛል።

ልክ በ 1974 ከሊጉ ከመውረዱ በፊት የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ እንደ ሾመው ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ በወራጅ ቀጠናው ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ የነበሩትን ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ሾሟል።

አርጀንቲናዊው አሠልጣኝ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመጪው እሁድ ወደ አንፊልድ ተጉዘው ከሊቨርፑል ጋር ያከናውናሉ።

አጋራ

YouTube

አማEN