ማንችስተር ዩናይትድ ከወራጅ ቀጠናው መቼ ሊወጣ?
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ11 ጨዋታዎች ስምንት ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ ከታች ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ፤ ከመውረድ ስጋት ለመትረፍ በመጪው ጥር የዝውውር መስኮት 150 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ማድረግ ይጠበቅበታል ተባለ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
በአንፊልድ በሊቨርፑል 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ 34 ግቦችን በማስተናገድ በአውሮፓ አምስት ታላላቅ ሊጎች የከፋ የተከላካይ ክብረውሰን የተመዘገበበት ማንቸስተር ዩናይትድ፤ ቀጣዩን የውድድር ዘመን በቻምፒዮንሺፕ የማሳለፍ ከባድ ስጋት ተጋርጦበታል።
ክለቡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት 150 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥቶ ካርሎስ ባሌባን፣ አንድሬ ሳንቶስን እና ዩሪ ቲሌማንስን ቢያስፈርምም፣ የተከላካይ እና የአጥቂ መስመሩን በበቂ ሁኔታ ባለማጠናከሩ እንዲሁም የማርከስ ራሽፎርድ፣ የሉክ ሾው እና የቤንጃሚን ሴስኮ ጉዳቶች በቡድኑ ላይ ከባድ ጫና ፈጥረዋል።
ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትድ 1.1 ቢሊዮን ፓውንድ እዳ ቢኖርበትም፣ በፕሪሚየር ሊጉ አዲስ የወጪ ገደብ ህግ መሰረት እና ባለፈው ዓመት 677.6 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ በማስመዝገቡ በጥር ወር ተጫዋቾችን ለማስፈረም የገንዘብ አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ቻምፒዮንሺፕ መውረድ ከ150 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የቀጥታ ገቢ ማጣት እና ከፍተኛ የንግድ ኪሳራ ስለሚያስከትል፣ አዲሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ቡድኑን ለማዳን የዝውውር ድጋፍ ማግኘት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።
