ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በህዝባችን በፊት ጨዋታውን ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል: አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 4ኛ ጨዋታ ነገ በባህርዳር ስታዲየም ከሞዛምቢክ ያደርጋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 5

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ከወሳኙ ጨዋታ በፊት በሰጡት ሀሳብ የራሳችንን ዕድል በራሳችን ለመወሰን ወደ ሜዳ እንገባለን ብለዋል።

አሰልጣኙ ጨዋታውን በሜዳችን እና ደጋፊያችን ፊት የምናደርግ በመሆኑ ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ጨዋታው ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ወሳኝ በመሆኑ መከላከልን መርጠን ወደ ሜዳ አንገባም በለዋል አሰልጣኙ።

በመጀመሪያው ጨዋታ ጉዳት ላይ የነበሩት ቸርነት ጉግሳ እና ብርሀኑ በቀለ ከጉዳታቸው መመለሳቸውንም ተናግረዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN