ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ቢያትሪስ ችቤት በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ መሆኗ ተገልጿል

የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት በ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ.በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ውድድር ላይ ትገኛለች። ቼቤት ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ይህ የመጀመሪያ ይሆናል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ቼቤት በ2023 በባትረስ በተካሄደው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የ10 ኪ.ሜ. ውድድርን ያሸነፈች ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በኋላም በቤልግሬድ የቻምፒዮንነት ክብሯን አስጠብቃለች።

በዚያው ዓመት በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ በ5,000 ሜትር እና በ10,000ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያጠለቀች ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት በቶኪዮ በተካሄደው የ2025 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም በተመሳሳይ ርቀቶች ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።

በተጨማሪም በ2024ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን የሰበረች ሲሆን፤ የመጀመሪያው በ10,000 ሜትር 28 ደቂቃ ከ54.14 ሰከንድ ፣ በሁለተኛው ደግሞ በ5 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር 13 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ነው። በ2025 ደግሞ በ5,000 ሜትር 13 ደቂቃ ከ58.06 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ ርቀቱን ከ14 ደቂቃ በታች የሮጠች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት መሆን ችላለች።

ቢያትሪስ በ2026 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ስለ ኢትዮጵያ ጉዞዋ በሰጠችው አስተያየት፣ ስለ ውድድሩ ብዙ ስትሰማ የነበረችውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአካል ለመመልከት ከፍኛ ጉጉት እንዳላት ገልጻለች።

አጋራ

YouTube

አማEN