ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ኢትዮጵያ በአራት ወራት ከቡና 1.16 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ 1.16 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት ከሐምሌ እስከ ጥቅምት ባሉት አራት ወራት ውስጥ 167.8 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ተልኳል።
ይህ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ24.6 ሺህ ቶን እንዲሁም በገቢ የ157.2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል።
የተመዘገበው ስኬት ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነትን ለማስፋትና የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ያላሰለሰ ጥረት የሚያመላክት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። አክለውም ለዚህ ውጤት መመዝገብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አጋራ

YouTube

አማEN