ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ከ5 ወራት በኋላ የመጀመሪያው የመም ውድድር በአዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀመረ

6ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ሲጀመር በቀጣይ ቅዳሜ ህዳር 19 ፍፃሜውን ያገኛል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

የአጭር ፣ መካከኛ፣ መሰናክል እና የሜዳ ተግባር ውድድሮች እያካሄደ የሚገኘው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ100ሜ ጀምሮ እስከ 1500ሜ እና 3 ሺህ መሰናክል ውድድሮች ይካሄዳሉ።

አትሌቶች ራሳቸውን የሚያዩበት፣ ክለቦች አዳዲስ አትሌቶችን የሚቀጥሩበት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀጣይ ወር ለሚያደርገው የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር ራሳቸውን የሚፈትሹበት ነው።

በባለፈው ሰኔ ወር የክለቦች የአጭርና መካከለኛ ውድድር ያካሄደው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ5 ወራት በኋላ የ2019 የመጀመሪያ ውድድሩን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

በአንደኛ እና በሁለተኛ ዲቪዚዮን አጠቃላይ 16 ክለቦች እየሳተፉ ይገኛል። በመክፈቻው ቀን በ100ሜ እና 400ሜ የፍፃሜ ውዶድሮች ሲካሄዱ፣ 100ሜ መሰናክል፣ 800ሜ እና በሌሎችም የማጣሪ ውድድሮች ተካሂደዋል። በውድድሩ 271 ወንድ አትሌቶች በሴቶች ደግሞ 157 በአጠቃላይ 407 አትሌቶች ተሳታፊ ናቸው።

በውድድሩ በሴት እና በወንድ እንዲሁም በአጠቃላይ የዋንጫ አሸናፊ ሽልማት ይካሄዳል።

አጋራ

YouTube

አማEN