ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የታይዋን ከቻይና ጋር ዳግም መዋሃድ አይቀሬ መሆኑን ሺ ጂንፒንግ ገለጹ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ታይዋንን ከእናት ሀገሯ ቻይና ጋር በሰላማዊ መንገድ ዳግም የማዋሃድ የታሪክ ጉዞ ሊገታ የማይችል ማዕበል ነው ሲሉ አስታወቁ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ፕሬዚዳንት ሺ የቻይናው አብዮታዊ መሪ ሰን ያት-ሴን 160ኛ የልደት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር የታይዋን ጉዳይ እልባት ማግኘት የኮሚኒስት ፓርቲው የማይናወጥ ታሪካዊ ተልዕኮ መሆኑን ጠቅሰው በ“አንድ ሀገር ሁለት ሥርዓት” ማዕቀፍ ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ የታይዋን መንግሥት ጥሪውን ውድቅ በማድረግ ሕዝባቸው ለኮሚኒስት ፓርቲው አገዛዝ እንደማይገዛ አስታውቋል።

ይህ ንግግር የተደመጠው ታይዋን 29 የቻይና የጦር አውሮፕላኖችና መርከቦች በደሴቲቱ ዙሪያ ጥበቃ እያደረጉ መሆኑን ባስታወቀችበት ወቅት ነው። በተጨማሪም ሺ ጂንፒንግ በቀጣይ ሳምንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት የኤፔክ (APEC) ጉባኤ ዋዜማ ላይ የተሰማ መሆኑ ትኩረትን ስቧል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

አጋራ

YouTube

አማEN