ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለ አምስት ኮከብና የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተሰኘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ2027ቱ የአፔክስ (APEX) ባለ አምስት ኮከብ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች አንዱ ሆኖ ዕውቅና ከማግኘቱም ባለፈ የአፔክስ የአፍሪካ አጠቃላይ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

አየር መንገዱ ያገኛቸው እነዚህ ታላላቅ ዕውቅናዎች በዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎቹ ሁሉ ምቹ፣ አስተማማኝና አስደሳች የጉዞ ልምድ ለመስጠት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቁ መሆናቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ዕውቅናዎቹ አየር መንገዱ ለላቀ ደረጃ፣ ለልዩ አገልግሎትና የእያንዳንዱን መንገደኛ ጉዞ በቀጣይነት ለማሻሻል ያለውን ትጋት በድጋሚ የሚያረጋግጡ መሆናቸው ተመላክቷል። አየር መንገዱ ከእርሱ ጋር ለሚበሩና የጉዞው አካል ለሆኑ መንገደኞችም ምስጋናውን አቅርቧል።
አጋራ

YouTube

አማEN