
ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል!!! | ናብሊስ
ግንቦት 27, 2017 · 50:31 9K
ስንፍና አንድን ነገር ማድረግ እየቻልን አቅሙ እያለን ምን መደረግ እንዳለበት እያወቅን ስራውን ለመከወን ፍቃደኛ አለመሆን ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ገፊ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ ሥራን ለነገ ማለት እንደ ስንፍና ይቆጠራል፡፡ በዚህ ሳምንት በናብሊስ መሰናዷዋችን “ስንፍና” በሚል ርዕስ ውይይት አድርገናል ተከታተሉን ፡፡ ለማንኛውም ሀሳብ፣ አስተያየት ወይም ጥያቄ በ 0929696969 በመደወል አልያም የፅሑፍ መልዕክት በማስቀመጥ ተሳተፉ ፡፡
