ሞዛምቢክ ከ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ይገናኛሉ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከነገ በስቲያ ሞዛምቢክን ወደ ማፑቶ ተጉዞ ይገጥማል። ሁለቱ ቡድኖች አርብ ዕለት የሚያደርጉት ጨዋታ በነጥብ ጨዋታ ሁለተኛው ፍልሚያቸው ሆኖ ይመዘገባል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 43

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከነገ በስቲያ ሞዛምቢክን ወደ ማፑቶ ተጉዞ ይገጥማል።
ሁለቱ ቡድኖች አርብ ዕለት የሚያደርጉት ጨዋታ በነጥብ ጨዋታ ሁለተኛው ፍልሚያቸው ሆኖ ይመዘገባል።
ከዚህ ቀደም በሀገር በቀል ተጨዋቾች ብቻ በሚደረገው የቻን ውድድር ላይ ተገናኝተው ነበር።
በአልጄሪያ በተስተናገደው የ 2022ቱ የቻን ውድድር ሁለቱ ሀገራት በምድብ ማጣሪያ ተገናኝተው ጨዋታቸውን ያለ ግብ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ ጨዋታውን ያደረገ ሲሆን ጋቶች ፓኖም እና ከንዓን ማርክነህ ብቻ ከዛ ስብስብ አሁንም ድረስ የሚገኙ ተጨዋቾች ናቸው።
የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ከአራት ዓመት በፊት ባሠለጠኑት ቺኪኒሆ ኮንዴ እየተመራ ጨዋታውን ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ ያደረጋቸውን ሁለቱንም ጨዋታዎች ሲሸነፍ ሞዛምቢክ በአራት ነጥብ እና በግብ ክፍያ ምድቡን እየመራች ትገኛለች።
አርብ እለት ሞዛምቢክ ከ ኢትዮጵያ በማፑቶ የሚያደርጉትን ጨዋታ የሀገሬ ቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት ያስተላልፈዋል።
