የ2026 የዓመቱ የዓለም ኮከብ ሴት አትሌት የመጨረሻ 3 ዕጩዎች ይፋ ሆኑ
በሞናኮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የመጨረሻ ዕጩ የሆኑት ሜሊሳ ጄፈርሰን ዉደን፣ ማሳይ ራስል እና ኦድሬይ ቬሮ የ2026 የዓመቱ የዓለም ኮከብ ሴት አትሌት ክብር የመጨረሻ ሶስት ተፎካካሪዎች ሆነው መመረጣቸዉን የአለም አትሌቲክስ ይፉ አድርጓል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 8

በሞናኮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የመጨረሻ ዕጩ የሆኑት ሜሊሳ ጄፈርሰን ዉደን፣ ማሳይ ራስል እና ኦድሬይ ቬሮ የ2026 የዓመቱ የዓለም ኮከብ ሴት አትሌት ክብር የመጨረሻ ሶስት ተፎካካሪዎች ሆነው መመረጣቸዉን የአለም አትሌቲክስ ይፉ አድርጓል።
በደጋፊዎች፣ በአትሌቶች፣ በሜዲያ አባላት እና በዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች በተደረገው ድምፅ አሰጣጥ መሠረት፣ እነዚህ ሶስት ዕጩዎች በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች ቡድን ከተመረጡት 10 እጩዎች መካከል ከፍተኛውን ድምፅ በማግኘት ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል።
ህዳር 19/2019 በሞናኮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ አሸናፊዋ አትሌት ትለያለች።
👉 ሜሊሳ ጄፈርሰን-ዉደን (አሜሪካ)
በአልቲሜት ሻምፒዮንሺፕ በ100 እና 200 ሜትር ድርብ ድል ያሳካችዉ ሜሊሳ ጄፈርሰን-ዉደን ከእጩዎቹ አንዷ ናት። ሜሊሳ በ100 ሜትር 10.62 ሰከንድ እንዲሁም በ200 ሜትር 21.47 ሰከንድ በመግባት የዓመቱን የዓለም የተሻለ ሰዓት አስመዝግባለች።

👉ማሳይ ራስል (አሜሪካ)
ሌላኛዋ አሜሪካዊት አትሌት ማይሳ ራስል የ200 ሜትር ሰዓቷም በዓለም ታሪክ 3ኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት ያደረጋት ሲሆን በ100 ሜትር መሰናክል የዓለም ክብረወሰንን 12.09 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች። አትሌቷ የውድድር ዘመኑ 10 ፈጣን ሰዓቶች መካከል 9ኙን ያስመዘገበች ሲሆን በውድድር ዘመኑ በ100 ሜትር መሰናክል ሽንፈት ያላስተናገደችዉ ማሳይ የአልቲሜት እና የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጭምር ናት።
👉ኦድሬይ ቬሮ (ስዊዘርላንድ)
በአልቲሜት፣ በዳይመንድ ሊግ እና በአውሮፓ የ800 ሜትር ሻምፒዮናን አሸንፋለች። አትሌቷ የዳይመንድ ሊግ ሪከርድን ሶስት ጊዜ ያሻሻለች ሲሆን፣ ሰዓቷንም ወደ 1:53.70 በማሻሻል የዓመቱን የዓለም የተሻለ ሰዓት በማስመዝገብ በዓለም ታሪክ 3ኛዋ ፈጣን አትሌት አድርጓታል።
