የዓይን ብርሃንን የመለገስ ሀገራዊ ዘመቻ ይፋ ሆነ
ብርሃናቸውን ያጡ ዜጎችን ዳግም ለማብቃት በተያዘው በጀት ዓመት 700 የዓይን ብሌኖችን ለመሰብሰብ እና 5 ሺህ በጎ ፈቃደኞችን ቃል ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ደምና ሕብረሕዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የዓይን ብሌን ልገሳ ወር ይፋ አድርጓል።
የጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ ሀጂ መስዑድ አደም እንደገለጹት የዓይን ብሌን መለገስ ሰውን ከፅልመት ወደ ብርሃን የሚያወጣና በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ የሚበረታታ የላቀ የሰው ወዳድነት መገለጫ ነው።
የባንኩ ም/ዋና ዳይሬክተር ጤናዬ ደምሴ በበኩላቸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ንቅለ ተከላ ዋነኛው አማራጭ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡ ፈቃደኝነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። ወሩን አስመልክቶም የሃይማኖት አባቶች ውይይትና የሚዲያ ዘመቻዎች ይከናወናሉ ተብሏል ሲል ፋና ዘግቧል።
