የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ውጤት
የ2027ቱ ቶታል ኢነርጂስ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ትናንት ሰኞ ሲቀጥሉ፤ ጋና ሶማሊያን በማሸነፍ የማለፍ ተስፋዋን ስታለመልም ጊኒ ከሜዳዋ ውጪ ኤርትራን ረታለቸ፣ ቤኒን ደግሞ በመጨረሻ ደቂቃዎች ግብ ድል አስመዝግባለች።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 17

👉ሶማሊያ 0 – 1 ጋና
በሜዳዋ ሶማሊያን ያስተናገደችዉ ጋና 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፋለች። ጥቋቁር ከዋክብቶቹ ሶስት ነጥብ እንዲያገኙ ያስቻላቸው ብቸኛ ግብ ጆርዳን አዩ በ36ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
ባለፈው ጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት ስቶ የነበረው አዩ፣ በዚህኛዉ ጨዋታ ግን የተገኘዉን እድል ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን ለድል አብቅቷል። በዚህም ውጤት መሰረት ጋና ነጥቧን ወደ 6 ከፍ በማድረግ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሶማሊያ በበኩሏ ምንም ነጥብ ሳትይዝ ከወዲሁ ከማጣሪያው ውጪ ሆናለች።
👉ኤርትራ 1 – 3 ጊኒ
ግብፅ ካይሮ በሚገኘው አል ሰላም ስታዲየም ኤርትራ የሜዳ ጨዋታዋን አድርጋ በጊኒ ተሸንፉለች። 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈቸዉ ጊኒ በምድብ አራት ወደ መሪነት መታለች።
ለጊኒ ሞሀመድ ሶማህ አንድ፣ ያኩባ ባሪ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል። የኤርትራን ብቸኛ ግብ የቀድሞ የሀዋሳ ከነማ አጥቂ አሊ ሱሌማን በጨዋታው ማጠናቀቂያ ጭማሪ ሰአት ላይ አስቆጥሯል። ጊኒ ነጥቧን ወደ 9 ከፍ አድርጋለች።
👉መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ 0 – 1 ቤኒን
በካሜሩን ዱዋላ በተደረገ ሌላኛዉ የምድብ ጨዋታ ቤኒን ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ጨዋታው ያለ ግብ ሊጠናቀቅ የነበረ ቢሆንም፣ ኤደ ኦሎኮ ጨዋታው ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ደቂቃ(90+3) ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቤኒን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝታለች። ቤኒን ነጥቧን ወደ 10 ከፍ በማድረግ የምድብ 6 መሪ ሆናለች።
