ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 32ኛው የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ውድድር ተጠናቀቀ

30 ቡድኖች ባለፉት ሦስት ወራት በቢቮፍቱ ከተማ በተሳተፉበት የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ውድድር የቢሸፍቱ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር ከ40 እና ከ50 ዓመት በላይ አሸናፊ ሲሆን ይህም ከ10 ዓመታት በፊት የሰራውን ታሪክ እንዲደግም አስችሎታል

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 19

በሶስት የዕድሜ ምድብ ከ35፣ ከ40 እና ከ50 ዓመት በላይ በ30 ቡድኖች መካከል ለሶስት ወራት ሲካሄድ ቆይቷል።

30 ቡድኖች ባለፉት ሦስት ወራት በቢቮፍቱ ከተማ በተሳተፉበት የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ውድድር የቢሸፍቱ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር ከ40 እና ከ50 ዓመት በላይ አሸናፊ ሲሆን ይህም ከ10 ዓመታት በፊት የሰራውን ታሪክ እንዲደግም አስችሎታል

የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ፍፁም ሳህሉ የጤና ስፖርት ውድድሮች ዜጎች አካላዊ ብቃታቸውን እንዲጠብቁ ከማድረጉ ባሻገር እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ በማድርግ ረግድ የማይተካ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብራንድ ስራ አስኪያጅ አቶ አመሀ ኪዳነማሪያም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት ከፍተኛ ገንዘብ ካፈሰሰባቸው ዘርፎች መካከል የጤና እና ስፖርት ዘርፍ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አንስተው እንዲህ አይነት ጉዳዮች ተተኪ ስፖርትኞን ለማፍራት እና ሀገርን ለማስጠራት ትልቅ ፋይዳ ያላቸው በመሆናቸው ባንኩ የሚጠበቅበትን እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በጤና ስፖርት ማህበር ውድድሩ የተሳተፉ ተጨዋቾችም መሰል መድርኮች ጤናን ከመጠብቅ አንጻር ትልቅ ትርጉም ያላቸው በመሆኑ ተጠናከርው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN