ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

አንድ ቢሊየን ዩሮ የውል ማፍረሻ ለቫልቬርዴ!

ፌዴ ቫልቬርዴ በሪያል ማድሪድ እስከ 2031 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም ነው።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

አዲሱ ስምምነት በ 2029 ክረምት በሚጠናቀቀው የኡራጓዊው ኢንተርናሽናል ነባር ኮንትራት ላይ ተጨማሪ ሁለት የውድድር ዘመናትን ይጨምራል ተብሏል።

ክለቡ ለኮከብ ተጫዋቾቹ እንደሚያደርገው የተለመደ አሰራር ሁሉ ይህም የቫልቬርዴ ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ አንቀጽ እንደሚካተትበት ይጠበቃል።

አዲሱ የኮንትራት ውል የደመወዝ ጭማሪ የሚያስገኝለት ሲሆን በቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑ ተጫዋቾች ተርታ ያሰልፈዋል።

ማድሪድ ይህንን ስምምነት ያቀረበው የቡድኑ አምበል የሆነው ቫልቬርዴ በአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ስር እያሳየ ላለው ድንቅ ብቃት እና በስፔኑ ክለብ ላስመዘገበው ስኬታማ ጉዞ እውቅና ለመስጠት ነው።

ቫልቬርዴ በዚህ የውድድር ዘመን በ15 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሶስት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ፌዴ ከፔናሮል ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ በዋናው ቡድን 388 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ሁለት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ 14 ዋንጫዎችን አንስቷል።

በላሊጋው ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ በነገው ዕለት በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናቦ ሴልታ ቪጎን ያስተናግዳል።

አጋራ

YouTube

አማEN