የማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የቤት ስራዎች!
ለአዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የክለቡ ባህል ፣ የመከላከል ክፍሉ ክፍተት እና የፈርናንዴዝ ኮንትራት ቀዳሚ ተግባራቸው ይመስላሉ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ለፖቼቲኖ የተረከቡት ስራ ትልቅ ፈተናን ያዘለ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ በደረጃ ሰንጠረዡ 18ኛ ላይ ይገኛል። ነገ ከሰዓት በኋላ የሚደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ደግሞ ምናልባት በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ።
ለአርጀንቲናዊው አሠልጣኝ በኦልድትራፎርዱ ክለብ ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ክለቡን ተፎካካሪ ማድረግ የሚችል ባህል መፍጠር ነው።
ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ በዚህ የውድድር ዘመን ዩናይትድ ድክመት ያሳየባቸውን የሜዳ ላይ ክፍሎች መጠቆም ቀላል ሊሆን ይችላል። ሆኖም ይኸው ተመሳሳይ የተጫዋቾች ስብስብ ባለፈው የውድድር ዘመን በቅርቡ በተሰናበቱት ማይክል ካሪክ አማካኝነት ተለውጦ በፕሪሚየር ሊጉ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሻምፒዮንስ ሊግ ማለፉ ፈጽሞ ሊዘነጋ አይገባም ብሏል።
ለፖቼቲኖ በጣም አፋጣኝ ከሆኑት ተግባራት አንዱ በደረሰባቸው ጫና ምክንያት የታሰሩ የሚመስሉትን የተጫዋቾች አስተሳሰብ መቀየር ይሆናል።
”አሁን ያለውን ሁኔታ ብቻ ማየት ስህተት ነው” ያሉት ፖቼቲኖ “የዚህን ክለብ ትልቅ አቅም ማየት አለብን። ይህ ጨዋታ መሆኑን መረዳት አለብን ፤ ከጨዋታው ጋር ለመዋሃድ ደግሞ ነፃነት ሊሰማን ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ሌላኛው ፖቼቲኖ መፍትሄ ሊሰጡት የሚገባው ቦታ የዩናይትድ የመከላከል ክፍል ይመስላል። የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ክፍል በአውሮፓ ታላላቆቹ አምስት ሊጎች ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ክፍል ነው። ይህንን መቀየር ትልቁ የፖቼቲኖ የቤት ስራ መሆኑ አይቀርም።
በአዲሱ የውድድር ዘመን አቋሙ የወረደው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበለትን የኮንትራት ማራዘሚያ ውድቅ አድርጓል። በብሩኖ ዙሪያ ያለውን ያልጠራ ከባቢ ማደስም የአርጀንቲናዊው አሠልጣኝ ሌላ የቤት ስራ እንደሚሆን ይጠበቃል።
