ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

“ዊሊያም ሳሊባ ለጨዋታው ዝግጁ ነው” ሚኬል አርቴታ

የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች መልስ በቡድኑ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን የአካል ብቃት እና በተመለከት በሰጠው ሃሳብ ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ ከረጅም ጊዜ የጀርባ ጉዳት አገግሞ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ በተቃራኒው ማርቲን ዙቢሜንዲ ደግሞ ለጥቂት ሳምንታት በጉዳት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኙ አሳውቋል፡፡

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 10

በሌላ በኩል ለስምንት ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል ተብሎ የሚጠበቀው ቡካዮ ሳካ አሁንም ወደ ቡድኑ ለመመለስ የተወሰነ ጊዜ ይቀረዋል ብሏል፡፡

አርሰናል በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጪ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚጫዎት ሲሆን ብሩኖ ጊማሬሽ የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡ አርቴታ የቀድሞው የማግፓይስ አምበል በሴንት ጀምስ ፓርክ መልካም አቀባበል እንደሚደረግለት ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል፡፡

ከ10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 27 ነጥብ የሰበሰበው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ባለፈው ዓመት በዚህ ሰዐት ከሰበሰበው ነጥብ በሁለት ነጥብ ክፍ ብሎ መቀመጡ ተጫዋቾቹ በእያንዳንዱ ጨዋታ እያሳዩት ባሉት የማሸነፍ ፍላጎት መሆኑን ተናግሯል፡፡

አጋራ

YouTube

አማEN