ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ራፋኤል ናዳል የሪያል ማድሪድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ተመረጠ

የቀድሞው የዓለም ቁጥር አንድ እና የ22ጊዜ ግራንድ ስላም ሻምፒዮኑ ራፋኤል ናዳል የሪያል ማድሪድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አዲስ አባል ሆኖ በይፋ ተመርጧል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

ናዳል በክለቡ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሰጡት ድምጾች 99.5 በመቶውን በማግኘት እና ከቀረቡት ዕጩ አባላት ትልቁን ድምጽ በማግኘት ነው የተመረጠው

ናዳል በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጭ ባለው ስብዕናው እንዲሁም የስፖርት እሴቶችን በማክበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አክብሮት እና አድናቆት አትርፏል ያሉት የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በተለይ ከማድሪድ ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት እንዲመረጥ አድርጎታል ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ ናዳል ቦርዱን መቀላቀሉ የሪያል ማድሪድን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የመገንባት ኃላፊነት እና ኩራት ለመጋራት መወሰኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ሪያል ማድሪድ ከወላጆች ወደ ልጆች የሚተላለፍ እና ሰዎችን የሚያስተሳስር ክለብ መሆኑን የገለጸው ናዳል፣ ክለቡ ዓለም አቀፍ ስም እና ታላቅነት ያለው በመሆኑ ወደፊትም በስኬታማነቱ እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚሰራ ተናግሯል።

አጋራ

YouTube

አማEN