ኒውካስትል ከ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ከፉልሀም
በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ሲደረጉ የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚገናኝበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 39

ማግኝት ከነበረበት 30 ነጥብ 27ቱን ያሳካው አርሰናል ሌላ ድል ለማግኝት ወደ ሴንት ጆምስ ፓርክ ስታዲየም በሚያመራበት ጨዋታ ከኒውካስትል ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል።
ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጠው ሀሳብ የማቲያስ ያስልን ፈተና በድል ለመወጣት እንጫወታልን ብሏል። ቡሩኖ ጉማሬሽ የቀድሞ ክለቡን በሚገጥመብት ጨዋታ ዊሊያም ሳሊባ ከጉዳቱ በመመለሱ ለጨዋታው ዝግጁ ሆኗል።
በተቃራኒው ማርቲን ዙቢሜንዲ በጉዳት ከስብስቡ ውጪ ሲሆን ቡካዮ ሳካ አሁንም ከጉዳቱ አላገገመም። ጨዋታው ምሽት 2 ሰዓት ከ 30 ላይ የሚጀመር ይሆናል።
ቀን 9 ሰዓት ከ 30 ላይ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ፉልሀምን ያስተናግዳል። በሊጉ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፉት ኢንዞ ማሬስካ ወደ አሸናፊነት ለመመልስ በሚያደርጉት ጨዋታ ባለፉት 4 ጨዋታዎች ካልተሸነፈው ፉልሀም ሌላ ፈተና የሚጠብቃቸው ይሆናል።
በጨዋታው አንቶኒዮ ሴሜኒዮ በጉዳት የማይሰለፍ ሲሆን የኮሳኖቭ እና ኑኔዝ መሰለፍም አልተረጋገጠም። ማርክ ጌሂ ግን ለጨዋታው ዘግጁ ሆኗል ተብሏል።
አስቶንቪላ ከ ሰንደርላንድ፣ ቦርንማውዝ ከኖቲንግሀም ፎረስት፣ ቶተነህም ሆትስፐርስ ከ ኢፕስዊች ታውን እና ኮቬንትሪ ከ ከሪስታል ፓላስ ሌሎች ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
