የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሩብ ዓመቱ ከ63 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን ገለፀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፍርድ ቤት በተወሰኑ መዝገቦች ከ63 ነጥብ 46 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ችሏል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ተቋሙ በሩብ ዓመቱ በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች በሚገኙ 8 ነጥብ 193 ቢሊዮን ብር መጠን ባላቸው 232 የፍትኃብሔር እንዲሁም 27 ነጥብ 772 ሚሊዮን ብር መጠን ባላቸው 27 የአሰሪና ሠራተኛ መዝገቦች ላይ የሕግ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
ከእነዚህ መካከል በ17 የፍትኃብሔርና በ4 የአሰሪና ሠራተኛ መዝገቦች ላይ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን፣ በዚሁ ውሳኔም ከ63 ነጥብ 46 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ማዳን ተችሏል።
በተጨማሪም በከፍተኛ የኃይል መስተላለፊያ መስመሮች ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ስርቆት በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የክስ አቤቱታ የማቅረብ፣ የከሳሽነት እና የሙያ ምስክርነት ቃል የመስጠት ሥራ ተከናውኗል። በስርቆቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ያደረሱት ጉዳት ግምታዊ የገንዘብ መጠን 2 ነጥብ 369 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተመላክቷል።
