“ለታላላቅ ጉባኤዎች ሰላማዊ ፍጻሜ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው” – ኮሎኔል ጀነራል ደመላሽ
በቀጣይ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቁ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል መከረ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት ከተቋሙ፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ውይይቱን የመሩት የፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ነገ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 26ኛው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል።
ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሚካሄደው 5ኛው የአፍሪካ ሕዝብ ጤና ኮንፈረንስ የፀጥታና ትራፊክ ሥራዎች በጠንካራ የጋራ ቅንጅትና በጥብቅ ዲሲፕሊን መመራት አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል።
ለ21ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ለአፍሪካ ሕብረትና ለCOP32 ጉባኤዎችም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል። ግብረ-ኃይሉም ሕብረተሰቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።
