የኢትዮጵያ አየር ኃይል 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጎዳና ላይ ሩጫና በተለያዩ ኩነቶች እንደሚከበር ተገለፀ
ሀገርን የመጠበቅና ጥቃትን በድል የመመከት ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ ኩነቶች እንዲሁም የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚያከብር ተገለጸ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

አየር ኃይል እየተዋጋ ሀገርን የማልማትና ተቋም የመገንባት ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ በዓሉ እየተከበረ እንደሚቀጥል የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ተናግረዋል።
ባለፈው በ2018 ዓ.ም ለቢሾፍቱ እንደ መለያ የተጀመረው ይህ ውድድር፣ ሁለቱን የሀገር ኩራቶች ማለትም አየር ኃይልንና ታዋቂ አትሌቶችን በአንድ መድረክ ለማገናኘት ያለመ ስለመሆኑም ተገልጿል።
በሩጫው ሰራዊቱ ከማህበረሰቡ ጋር የሚሳተፍ ሲሆን፣ ከ10 ሺህ በላይ ህዝብና ከ800 በላይ ኤሊት አትሌቶች ይካፈላሉ ተብሏል። በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ እስከ 5ኛ ለሚወጡ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፣ 1ኛ 500 ሺህ፣ 2ኛ 250 ሺህ፣ 3ኛ 150 ሺህ ብር እንዲሁም ለ1ኛ አሸናፊዎች አሰልጣኞች እያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ አትሌቶችና መላው ህብረተሰብ ህዳር 20 ቀን በቢሾፍቱ ተገኝተው፣ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ የአየር ኃይልን 91ኛ የምስረታ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
