ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በአንድ ዓመት ውስጥ ከ120 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ120 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወነው 5ኛው ዙር ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ዘመቻ፣ በአጠቃላይ 120 ሺህ 205 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከተመለሱት ዜጎች መካከል 105 ሺህ 470 ወንዶች፣ 13 ሺህ 482 ሴቶች እና 1 ሺህ 253 ሕፃናት ሲሆኑ፣ 4 ሺህ 989 የሚሆኑት ደግሞ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

የመመለስ ሥራው በሳዑዲ ዓረቢያ በከባድ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ የተከናወነ ሲሆን፤ ተመላሾቹ በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊው ሰብዓዊ እንክብካቤና ድጋፍ ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራ ተከናውኗል።

ይህም መንግሥት በውጭ ሀገር በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቹ ጥበቃ ለማድረግ እና በሀገር ውስጥ መልሶ ለማቋቋም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

አጋራ

YouTube

አማEN