ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ለሶስት ወራት መሻሻል ያላሳየው ቼልሲ!

በአሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ ባለፉት ሶስት ወራቶች ወጥ አቋም ማሳየት ተስኖት ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እያስተናገደ ይገኛል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ቼልሲ በዓመቱ መጀመሪያ ፉልሃም እና ብራይተንን ሲያሸንፍ ያሳየው በጎሎች የታጀበ ውብ የማጥቃት አቀራረብ ቢያስወድሰውም ውጤቱ ግን ዘለቄታ አልነበረውም።

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሰማያዊዎቹ ባደረጓቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት ሦስት ጊዜ ብቻ ሲሆን አምስት ጊዜ ተሸንፈዋል። ባሸነፉባቸው ጊዜያትም አብዛኛውን ጊዜ አሳማኝ ብቃት አላሳዩም።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቦርንመዝ ፣ ኤቨርተን እና ማንችስተር ዩናይትድን ያሸነፈባቸው መንገዶች የቡድኑን ሙሉ አቅም በጉልህ ያሳዩ ናቸው ተብሎ አይታመንም።

ቼልሲ በቶተንሃም ፣ በሰንደርላንድ እና ሊድስ በተከታታይ ሽንፈት ሲያስተናግድ አንድ ነጥብ እንኳን የሚገባው እንቅስቃሴ አላሳየም።

ያለ ፍጹም ቅጣት ምት በሚቆጠር የግብ ዕድል መለኪያ መሠረት ካደረጓቸው 11 የሊግ ጨዋታዎች ውስጥ የበላይነት መውሰድ የቻሉት በአራቱ ላይ ብቻ ነው።

ለሰማዊያዎቹ ​አሳሳቢው ጉዳይ ከሽንፈቶቹ በላይ ከአሎንሶ ቡድን የሚታዩ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች በጣም ጥቂት መሆናቸው ነው።

አሁን ላይ የቼልሲ ዋነኛ ችግር በአካል ብቃት እጅግ ደካማ መሆኑ ይመስላል። በሊጉ ጅማሮ ጨዋታዎችን ያሸነፉባቸው እነዚያ ፈጣን አጀማመሮች ለዓይን የሚስቡ ቢሆኑም በተቃራኒው ደግሞ በጨዋታዎች መገባደጃ ላይ አቅማቸው እየተሟጠጠ ይሄዳል።

ከብሬንትፎርድ፣ ከቶተንሃም እና ከሊድስ ጋር በተሸነፉባቸው ጨዋታዎች ከተቆጠሩባቸው ዘጠኝ ግቦች ውስጥ ስምንቱ የተቆጠሩት በሁለተኛው አጋማሽ ነው።

ለጊዜው ቼልሲ የወሳኝ ተጨዋቾች ጉዳትን ጨምሮ በሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ በብዙ እየተፈተነ ይገኛል ከምንም በላይ ግን ባለፉት ሶስት ወራት ቡድኑ አንድም መሻሻል አለማሳየቱ ጥያቄዎችን መፍጠሩ አይቀርም።

አጋራ

YouTube

አማEN