“ሌባ ዳኛ አንፈልግም” – ኢሳያስ ጅራ
የብሪትሽ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የወጣት ዳኞች ልማት ፕሮጀክት ስልጠናን መስጠት ጀምሯል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

በስልጠናው ላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዳኞች ኮሚቴ የተመረጡ 30 ዳኞች ስልጠናውን መውሰድ ጀምረዋል።
በወጣት ዳኞች ላይ መስራት በወደፊቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ መስራት ነው በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ 17 ህጎችን መተርጎም ሳይሆን ህሊናውን ማስተዳደር የሚችል ዳኛ እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሌባ ዳኛ አንፈልግም ሲሉ ተናግረዋል።
በችግር ውስጥ የዳኝነት ህግ እንዴት እንደሚተገበር ማስተማር አለብን ሲሉ አክለው ተናግረዋል። የሴኔጋል እና የሞሮኮ የአፍሪካ ፍፃሜ ጨዋታ የካስ ውሳኔን ያስፈለገው የዳኞች ችግር ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ ህግ እና ስነምግባር ወጣት ዳኞች መማር አለባቸው ብለዋል።
በዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት 30 ዳኞች የሰለጠኑትን ስልጠና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለሚገኙ እና ዕድሜያቸው ከ14 አመት ጀምሮ ለሚገኙ ታዳጊዎች ለማሰልጠን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
