ሮናልዶ 986ኛ ጎሉን ቢያስቆጥርም አል ናስር በአል-አህሊ 3ለ1 ተሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ 986ኛ ጎል በማስቆጠር ወደ ታሪካዊው የ1,000 ጎሎች ምዕራፍ ቢቃረብም፣ ቡድኑ አል ናስር ባደረገው የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ በአል-አህሊ 3 ለ 1 ተሸነፈ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 4

ጨዋታው በተጀመረ በ14ኛው ደቂቃ የ41 ዓመቱ ሮናልዶ አል ናስርን መሪ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አል ናስር የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ ሮናልዶ ወደ ግብነት ሳይቀይረዉ ቀርቷል። የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት አል-አህሊ በጋሌኖ ግብ 1ለ1 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
አል-አህሊ በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን በመቆጣጠር በ71ኛው ደቂቃ ኢቫን ቶኒ፣ በ75ኛው ደቂቃ ደግሞ ሮጀር ኢባኔዝ ባስቆጠሯቸዉ ግቦች አል-አህሊን 3ለ1 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አል ናስር በ2026–27 የውድድር ዘመን ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዶ በደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃ ላይ እንዲቆይ አድርጎታል። ሮናልዶ በበኩሉ የ1,000 ጎሎች ታሪክ ለመጻፍ 14 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል። አል ሂላል የሊጉ መሪ ነዉ።
