ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ሴኔጋል ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ለማረጋገጥ የተቃረበችበትን ውጤት አስመዘገበች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚገኝበት የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ የምትገኝው ሴኔጋል ሱዳንን 4 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ለማረጋገጥ ተቃርባለች።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 7

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት የምድብ ተቀናቃኞቻችን ያደረጉት ጨዋታ በበርካታ ግቦች የታጀበ ሆኖ ተጠናቋል።

በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ፍጹም የበላይነትን ይዛ የነበረችዉ ሴኔጋል፡ በኒኮላስ ጃክሰን እና ኤል ሀጂ ማሊክ ዲዩፍ ግቦች መሪነትን ወስዳ ነበር።

ይሁን እንጂ ሱዳን በሁለተኛዉ አጋማሽ ላይ በጠንካራ አቋም ወደ ጨዋታ ተመልሳ በአል-ጎዞሊ ኑህ የ52ኛ ደቂቃ እና በሰላሀልዲን አዲል የ75ኛ ደቂቃ ግቦች ውጤቱን 2 ለ 2 በማድረግ አቻ መሆን ችለው ነበር።

ምንም እንኳ ሱዳን አስደናቂ ዉጤት ብታሳይም በመጨረሻ የሴኔጋል አጥቂዎች በተከታታይ ያስቆጠሯቸዉ ግቦች ጨዋታውን ቀይሮታል።

ፓቴ ምቡፕ በ87ኛው ደቂቃ ድንቅ ጎል በማስቆጠር ሴኔጋልን ዳግም መሪ ሲያደርግ፣ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ በጭማሪ ሰአት ፓውል ሜንዲ አራተኛውን ግብ በማስቆጠር የጨዋታዉን ፍጻሜ 4 ለ 2 አድርጎታል።

ዉጤቱን ነገ ከሞዛምቢክ ጋር ለሚጫወተዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተሻለ እድል የሚሰጥ ነዉ። ከአራት ጨዋታዎች 10 ነጥብ የሰበሰበችው ሴኔጋል ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ የሚበቃት ይሆናል።

ዋልያዎቹ በምድብ 4ኛ ጨዋታ ነገ 10:00 ላይ በባህር ዳር ከሞዛምቢክ ጋር የሚጫወቱ ሲሆኑ ተጠባቂውን ጨዋታ ሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ ወደ ተመልካቾች የሚያደርስ ይሆናል።

አጋራ

YouTube

አማEN