ሽንፈት ለነገው ድል የቤት ስራችንን እንድንሰራ ማሳያችን እንጂ የመጨረሻዎች መጨረሻ አይደለም: ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
የብሔራዊ ቡድናችን አባላት ድንቅ ጨዋታ ቢያሳዩንም የዛሬው ውጤት ግን አንዳሰብነው አልሆነም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ተመስገን ጥሩነህ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ መጨረሻው ድረስ ልዩ ድጋፋችሁን ለለገሳችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እና መላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው በማለት አመስግነዋል።
ዋሊያዎች ከዛሬው ጨዋታ በመማር በቀጣይ በተሻለ ውጤት ሕዝባችሁን እንደምታስደስቱ ሙሉ እምነት አለኝ በማለት ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩንህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህርዳር ስታዲየም ከሞዛምቢክ ያደረገውን ጨዋታ ቦቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።
