በአንድ ቀን ልዩነት ከባድ ጉዳት እና ዝርፊያ ያጋጠመው ዲዛየሬ ዱዌ
ፈረንሳዊው የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የፊት መስመር ተጫዋች ዲዛየሬ ዱዌ ቅዳሜ በሜዳ ላይ የደረሰበት ከባድ ጉዳት እንዲሁም በመኖሪያ ቤቱ የስርቆት ሙከራ ምክንያት ሁለት ጊዜ የከፋ ፈተና አሳልፏል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ
ዱዌ በፈረንሳይ ሊግ 1 በ11ኛ ሳምንት ጨዋታ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ከሜዳው ውጭ ኒስን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ፍልሚያ፤ በ32ኛው ደቂቃ ቡድኑን 2 ለ 1 መምራት የሚያስችል ግብ ካስቆጠረ ከጥቂት ደቂቃዎች የጉልበት ጅማት መበጥስ (ACL) ጉዳት ገጥሞታል::
ተጫዋቹ በጉዳቱ ምክንያት በቀሪው የ2026-27 የውድድር ዘመን በሙሉ ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል፡፡
ወጣቱ በዚያው ሌሊት ወደ ኦርዤቫል መኖሪያ ቤቱ ሲደርስ፣ በቤቱ ግቢ የስርቆት ሙከራ ለማድረግ የገቡ ሰዎች በውስጥ ሰዎች መኖራቸውን ሲያውቁ ማምለጣቸውን ተከትሎ ፖሊስ አካባቢውን ከቦ ተገኝቷል።
በዚህ ድርጊት የተነሳ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን በተጫዋቹ መኖሪያ ቤት የጸጥታ ጥበቃን በአስቸኳይ ያጠናከረ ሲሆን የቀድሞው የክለቡ ተጫዋች ኔይማርን ጨምሮ በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቦች ለዱዌ ማበረታቻ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። የዱዌ እና የክቪቻ ክቫራትስኬሊያ በጉዳት መርዘም በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የማጥቃት መስመር ላይ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል።
