“ኒኮላስ ፔፔ የዓይን ቀዶ ህክምና ያደረገው የፀሃይ ግርዶሽ አይቶ አይደለም” ቪያሪያል
አይቮሪ ኮስታዊው የቪያሪያል የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ ያደረገው የዓይን ቀዶ ህክምና የፀሐይ ግርዶሽን በመመልከት የተከሰተ ነው የሚለውን ወሬ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ
ፔፔ በጥቅምት ወር የዓይን ቀዶ ህክምና ማድረጉን ተከትሎ በሊቨርፑል እና በሪያል ማድሪድ ሽንፈት ያስተናገዱባቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ አምስት ጨዋታዎችን ማሳለፉ ይታወሳል።
ባለፈው ነሐሴ ፔፔ ያለመከላከያ የፀሐይ ግርዶሽን ሲመለከት የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ጉዳዩ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሲነገር ቆይቷል። ቪያሪያል ትላንት ባወጣው መግለጫ ግን ቀዶ ህክምናው አስቀድሞ ታቅዶ የተከናወነ እና ከፀሐይ ግርዶሽ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑን አረጋግጧል።
የ31 ዓመቱ ኒኮላስ ፔፔ በ2025-26 የውድድር ዘመን በ46 ጨዋታዎች ስምንት ግቦችን አስቆጥሮ 11 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ካመቻቸ በኋላ፣ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በ12 ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል። በአሰልጣኝ ኢኒጎ ፔሬዝ የሚመራው ቪያሪያልም አራት ድል፣ ሶስት አቻ እና ስድስት ሽንፈት በማስተናገድ በላሊጋው 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
