ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በጆዜ ሞሪኒሆ ስር የተሻሻለው ሪያል ማድሪድ!

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

ሪያል ማድሪድ በጆዜ ሞሪኒሆ መሪነት ያለፉትን አስር ተከታታይ ጨዋታዎች በሁሉም ውድድር በማሸነፍ ከ 2022 የውድድር ዘመን በኋላ ጥሩ አጀማመር ማድረግ ችሏል።

ጆዜ ሞሪኒሆ እና ሪያል ማድሪድ በፈረንጆቹ ጥቅምት 25 ወደ ካምፕ ኑ አምርተው ባርሴሎናን ከመግጠማቸው በፊት የስፔን ላ ሊጋ ዋንጫን የማንሳት እድል እንደሌላቸው በስፋት ይነገር ነበር።

ሪያል ማድሪድ ተጠባቂውን የኤል ክላሲኮ ፍልሚያ በማሸነፍ ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ማጥበብ ከመቻሉም በላይ በአዲሱ አሠልጣኙ ስር በተሻለ መልኩ የተቀናጀ መስሎ ታይቷል።

ጆዜ ሞሪኒሆ ትናንት ምሽት ቡድናቸው ፒኤስቪን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፋቸውን ተከትሎ በውድድር ዘመን ከ 18 ጨዋታዎች በኋላ 16ኛው ድላቸው ላይ መድረስ ችለዋል።

ሪያል ማድሪድ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ በሪያል ቤቲስ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ያስተናገዳቸው ያልተጠበቁ ሽንፈቶች የፈጠሩት ጥርጣሬ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በአመኔታ ተቀይሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ አሁን ጥንካሬያቸው ጎልቶ እየተነገረላቸው ይገኛል። ከጠንካራ የተከላካይ መሰረት በመነሳት ባለፉት ስምንት የውድድር ዘመናት ካደረጉት በላይ ጥራት ያላቸውን የግብ ዕድሎች እየፈጠሩ የሚገኙ ሲሆን በሁሉም ውድድሮች አስር ተከታታይ ድሎችን አስመዝግበዋል።

ሞሪንሆ በዚህ ክረምት ወደ ማድሪድ ሥራ ሲመለሱ ቡድናቸው ኳስ ሳይዝ ሲቀር የሚኖረውን መረጋጋት ማምጣት በቅድሚያ ከያዟቸው ዕቅዶች ውስጥ ዋነኛው ነበር።

እስካሁን ቁጥሮቹ ከሞሪንሆ ጎን ናቸው ከ13 ጨዋታዎች በኋላ በላሊጋው ሁለተኛውን ምርጥ የመከላከል ሪከርድ የያዙ ሲሆን ባለፉት ስድስት የውድድር ዘመናት ከነበረው ባነሰ መልኩ ለተጋጣሚዎቻቸው ዝቅተኛ ግብ ዕድሎችን የሚፈቅድ ቡድን መሆን ችሏል።

አጋራ

YouTube

አማEN