ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ወጪ ንግድ 130.99 ሚሊዮን ዶላር ያስገኙ ኩባንያዎች እውቅና ተሰጣቸው

በኢትዮጵያ የጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ወጪ ንግድ ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስመዘገቡ ስድስት ኩባንያዎች በድምሩ 130.99 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

ሽልማቱ የተበረከተው የኢትዮጵያ ጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማኅበር ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው 15ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ነው።

የቅባት እህሎች ዘርፍ ተሸላሚዎች (ጠቅላላ ገቢ፦ 48.46 ሚሊዮን ዶላር)

1ኛ. በላይነህ ክንዴ ግሩፕ፦ 24.45 ሚሊዮን ዶላር
2ኛ. አልያንስ ስታር ቢዝነስ ግሩፕ፦ 12.38 ሚሊዮን ዶላር
3ኛ. ዐቢይ ማስረሻ (ግሽ ማር ቢዝነስ)፦ 11.63 ሚሊዮን ዶላር

የጥራጥሬ ዘርፍ ተሸላሚዎች (ጠቅላላ ገቢ፦ 82.53 ሚሊዮን ዶላር)

1ኛ. አብርሃም አበበ ኢምፖርት ኤክስፖርት፦ 35.16 ሚሊዮን ዶላር
2ኛ. ኤም ኤስ ኤ ትሬዲንግ፦ 34.61 ሚሊዮን ዶላር
3ኛ. ላምፕሮስ ትሬዲንግ፦ 12.76 ሚሊዮን ዶላር

“የማይበገር ንግድ እና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለቶች” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር 15 እና 16 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢን ጨምሮ ከ17 ሀገራት የተውጣጡ አምራቾች፣ ገዢዎች፣ የፋይናንስ ተቋማትና አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN