ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ትንሹ ሃይሌን ለአለም የሚያስተዋዉቀው መፅሀፍ

ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ በሰባት አመቱ ምሩፅ ይፍጠርን ለመሆን አስቦ ወደ አትሌቲክስ በመግባት የኢትዮጵያን ሩጫ መቀየሩ፤ ሩጫን እንደ መሳሪያ በመጠቀም በርካታ ስራዎችን ሰርቷል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያውለበለበው ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ከሩጫው ጎን ለጎን ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞችን በተለያዩ ድርጅቶች ቀጥሮ ለሀገሩ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

በባዶ እግሩ ሲሮጥ የነበረው ትንሹ ሀይሌ እና አሁን ላይ ደግሞ ሀይሌ ማን ነው ለሚለው መልስ የሰጠ መፅሀፍ መሆኑን ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ተናግሯል።

መፅሀፉ የሚተርከው የኔን የልጅነት እና የሩጫ ህይወት ነው የሚለው ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ኢንጅነር፣ ዶክተር፣ ፓይለት እና ሌላ ህልም ላላቸው ህፃነት በሙሉ የሚሆን ነው ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ስመ ጥር የሆኑት ግለሰቦች ልጅ ሆነው ልጅነታቸው ምን ይመስል ነበር የሚለው ጉዳይ የሚታወቅ አይደለም ያለው ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ትንሹ ሀይሌ መፅሀፍ ወግ፣ ባህል፣ አኗኗር ጠብቆ የተሰናዳ መፅሀፍ ነው ብሏል።

መፅሀፉ ልጆት የኢትዮጵያ ጀግኖችን እንዲያውቁ የሚረዳ ሲሆን በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ በተመረጡ መፅሐፍ አካፋፋይ ድርጅቶች እንደሚገኝ ተገልፆል።

አጋራ

YouTube

አማEN