ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ኢትዮጵያ ለኮፕ 32 ፍትሐዊ ተሳትፎ ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች

ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 ጉባኤ ሁሉም ሀገራት ፍትሐዊ ዕድል እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የጉባኤው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በቱርኪዬ አንታሊያ ከሚካሄደው የኮፕ 31 የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የጋራ ግምገማ ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀ የሚኒስትሮች ከፍተኛ ውይይት ላይ ነው።

ግምገማው የተመዘገበውን እድገት በግልጽ መመዘን፣ የአፈጻጸም እንቅፋቶችን መለየትና የአየር ንብረት እርምጃዎችንና ድጋፎችን የሚያፋጥኑ አማራጮችን ማመላከት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ሁለተኛው የጋራ ግምገማ የተለያየ ኃላፊነት፣ አቅምና መነሻ ያላቸው ሀገራት ትልማቸውን ከፍ እንዲያደርጉና ምኞታቸውን እንዲያሳኩ ዓለም አቀፍ ትብብርን በተሻለ መልኩ ለማደስ ዕድል ይሰጠናል” በማለትም ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኮፕ 32 ጉባኤ ሁሉም ሀገራት ትርጉም ያለው ድምፅና ፍትሐዊ ዕድል እንዲያገኙ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN