ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የኢትዮጵያን አትሌቶች ፅናት በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ለምታስተናግደው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) እያደረገች ባለው ተሳትፎ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጽናት እንደ ዋነኛ የሀገር ገጽታ መገለጫ ዘርፍ ቀርቧል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የማሳያ ስፍራ ፓቫሊዮን ሀገሪቱን “የሻምፒዮኖች ምድር” በሚል መሪ ቃል እያስተዋወቀ ይገኛል። በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው የኢትዮጵያውያን ሯጮች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የሚያሳዩት የላቀ ብቃትና አይበገሬ ጽናት የግለሰቦች ስኬት ብቻ ሳይሆን የመላው ሀገሪቱ ጥንካሬ መገለጫ ነው።

ይህ የአትሌቶቻችን መንፈስ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራና በታዳሽ ኃይል ልማት የምታደርገውን ያላሰለሰ ጥረት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳየት እንደ ትልቅ መሳሪያ እያገለገለ መሆኑም ተመላክቷል።

አጋራ

YouTube

አማEN