ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

32ኛው ሲቢኢ የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ውድድር በመጪው እሁድ ይጠናቀቃል

30 የጤና ስፖርት ማህበራት ሲሳተፉበት የቆየው ሲቢኢ የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ውድድር ለፍጻሜ የደረሱ ቡድኖች እንደተለዩበት የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሞቴ አባላት በሰጡት መግልጫ ይፋ አድርገዋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ በቆየው ውድድር ከ40 ዓመት በላይ እና ከ50 ዓመት በላይ የጤና ስፖርት ማህበር አባላት የተሳተፉ ሲሆን በመጪው ዕሁድ ለፍጻሜ የደረሱት ቡድኖች ለዋንጫ የሚፎካካሩ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር ባለፉት ረጅም ዓመትታ ዜጎች ጤናቸው እንዲጠብቁ እና ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ በማድርግ ረግድ ትልቅ ሃላፊነቱን ሲወጣ የቆየ ሲሆን በመጪዎቹ ጊዜያትም የተሳታፊ ቁጥርን እንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳድግ እንደሚሰራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎቹ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

የእሁዱ የመዝጊያ መርሀግብርም የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የስፖርት ቤተሰቡ በሚገኝበት በቢሾፍቱ ከተማ ይጠናቀቃል ተብሏል።

አጋራ

YouTube

አማEN