የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ የፖሊስ መንደር ግንባታ አስጀመረ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአባላቱን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ያለመ ዘመናዊ የፖሊስ መንደር ግንባታ በሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር አስጀምሯል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ግንባታውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ሠራዊቱ ሕዝቡ የጣለበትን አደራ በብቃት እንዲወጣ የአባላቱን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መቅረፍ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠው ለ1 ሺህ 600 ቤቶች ሲሆን፤ ለግንባታ የሚውለውን መሬት የሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር በነፃ ማቅረቡ ተመላክቷል።
እንደዚህ ዓይነት የፖሊስ መንደር ግንባታዎች በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የክልል መንግሥታት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል ሲል የዘገበው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።
