ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የወቅቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተመርጠዋል፡፡
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 3

የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የወቅቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተመርጠዋል፡፡
ይህ አህጉራዊ እውቅና በ”አፍሪካ ሃይፐርስኬለርስ” እና “ዘ ሊትልስቴፕስ ግሩፕ” ይፋ የተደረገ ሲሆን ሚኒስትሯ የተመረጡት በቴሌኮም እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ነው።
ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ለዚህ ምርጫ የበቁት የቴሌኮም ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ አስተማማኝ የዲጂታል መሰረት በመጣል እና በቴሌብር አማካኝነት የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ለሀገሪቱ ዲጂታል ሽግግር ላበረከቱት የላቀ የአመራር ሚና እንደሆነ ተገልጿል።
