ጋና የቆሻሻ ክምርን በማጽዳት ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ልትፈጥር ነው
የጋና መንግሥት በመዲናዋ አክራ አግቦግብሎሺ በተባለ ስፍራ ለዓመታት የተከማቸውን አንድ ሚሊዮን ቶን አደገኛ ቆሻሻ የማጽዳትና ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠር ዘመቻ ጀመረ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 3

የጋና መንግሥት በመዲናዋ አክራ አግቦግብሎሺ በተባለ ስፍራ ለዓመታት የተከማቸውን አንድ ሚሊዮን ቶን አደገኛ ቆሻሻ የማጽዳትና ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠር ዘመቻ ጀመረ።
አካባቢው ከተለያዩ የበለጸጉ አገራት የሚገቡ ያገለገሉ አልባሳትና የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች የሚጣሉበት ግዙፍ የቆሻሻ ማከማቻ ሲሆን፤ በየቀኑ የሚቃጠለው ፕላስቲክና መርዛማ ኬሚካል በነዋሪዎችና በሠራተኞች ላይ ከባድ የጤና ቀውስ አስከትሏል።
ይህን ችግር ለመቅረፍ የተጀመረው የሦስት ወር የጽዳት ዘመቻ ቆሻሻውን ከመዲናዋ 50 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኝ አስተማማኝ ማከማቻ እያጓጓዘ ይገኛል።
መንግሥት በቆሻሻ ለቀቃ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን ወደ ዘመናዊ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ሥርዓት በማስገባት 20 ሺህ ቋሚ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ማቀዱንም አስታውቋል።
