ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

የግሪን ፊውቸር አፍሪካ ምዕራፍ ሁለት የመዝጊያ መርሃ ግብር ነገ ይካሄድ

በእንግሊዝ ኤምባሲ በብሪቲሽ ካውንስል እና በጀስቲሺያ ሚዲያ በትብብር የሚዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር በወጣቶች የሚመሩ የአየር ንብረት ፈጠራዎችንና የአረንጓዴ ሥራ ፈጠራን ዋና ትኩረት ያደርጋል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በአዲስ አበባ በሚካሄደው የመዝጊያ መድረክ ላይ የዲፕሎማሲ አካላት የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃና በዘላቂ ልማት ዘርፍ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ።

በመድረኩ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የወጣቶች አመራር አረንጓዴ ሥራ ፈጠራ እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች የሚነዱበት የፓናል ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

የእንግሊዝ ኤምባሲ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ጄሚ ማንስብሪጅ የብሪቲሽ ካውንስል ምክትል ዳይሬክተር መጽናናት፣ ሳህሌ ሥራ ፈጣሪዋና ተጽዕኖ ፈጣሪዋ ኤደን ሙሉ እና ሌሎች ተወካዮች በሚሳተፉበት መድረክ በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የአየር ንብረት ትብብር የወጣቶችን የፈጠራ አቅም እና የዲጂታል ሚዲያ ለአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ ማሳደግ ያለውን ሚና ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ተሳታፊዎች የሰሯቸው የአየር ንብረት ተስማሚ የንግድ ሥራዎችና የፈጠራ ውጤቶች በኤግዚቢሽኑ የሚቀርብ ሲሆን ወጣቶች በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን የፈጠራ አቅም ለማሳየት ዕድል የሚፈጥርላቸው ይሆናል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች በአጠቃላይ 7 ሚሊዮን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ለአሥሩ ምርጥ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማትና ለሌሎች ተሳታፊዎች ደግሞ የፋይናንስ ድጋፍን ያካትታል።

ዝግጅቱ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ COP32ን ለማስተናገድ በምትዘጋጅበት ወቅት የወጣቶችን ተሳትፎ የአረንጓዴ ሥራ ፈጠራንና የተቋማትን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

አጋራ

YouTube

አማEN