ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በአንታልያ እየተካሄደ ካለው COP31 ጉባኤ ጎን ለጎን ከተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን ጋር በCOP32 ዝግጅቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

በውይይታቸውም የUNEP የበካይ ጋዝ ልቀት ክፍተት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የመጣጣም ክፍተት ሪፖርቶች የCOP32 ዝግጅቶችን እንዴት ሊደግፉ እንደሚችሉ በተለይም የመጣጣም ክፍተቱን ለመቀነስ የሚያስፈልጉ ሀብቶችን በተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ታዳሽ ኃይልን ስለማስፋፋት እና ከፍተኛ ሙቀትን ጨምሮ ከከባድ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ተጽዕኖ አንጻር የከተሞችን ተቋቋሚነት ስለማጠናከር መክረዋል።
በዚሁ ወቅት ኢንገር አንደርሰን፣ የCOP32 ፕሬዚዳንትነት ለአዲስ አበባ የሚያስቀምጣቸውን ቅድሚያ ጉዳዮች በሚወስንበት ሂደት UNEP ድጋፉን ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
