ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

“ሰርክ አዲስ ብስራት የሚሰማባት አዲስ አበባ ዛሬም በሌላ ስኬት በሌላ አዲስ የድል ታሪክ ብቅ ብላለች” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለከተማዋ ሌላ ተጨማሪ ከፍታና የውበት መጎናፀፊያ የሚያላብስ፤ ውብ ገፅታ ብቻ ሳይሆን ምቾት የተላበሰ ዘመናዊ ሁለንተናዊ ግልጋሎት የሚሰጥ የቦሌ የኮሪደር ልማት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ዜና ክፍል · · 2 ደቂቃ ንባብ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ዋና ሥራዎች ይፋ አድርገዋል።

1. በኮሪደሩ የለሙ አካባቢዎች
• ከቦሌ መድኃኒዓለም – ጎላጉል – እስከ እንግሊዝ ኢምባሲ
• ከቦሌ መድኃኒዓለም – እስከ ሞኤንኮ
• ከቦሌ ትምህርት ቤት – እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር
• ከኢምፔሪያል ሆቴል – እስከ ሻላ መናፈሻ
• ከቺቺኒያ – እስከ ቦሌ ሩዋንዳ
• ከአደይ አበባ ስታዲየም – እስከ ቦሌ መንገድ
• የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ኔትወርክ

2. አጠቃላይ የልማት ስፋትና መሠረተ ልማት
• 57 ሄክታር የልማት ቦታ
• 17 ኪ.ሜ. የመንገድ ርዝመት
• 34.ኪ.ሜ. የእግረኛ መንገድ
• 8 ኪ.ሜ. የሳይክል መንገድ
• 3 የተሽከርካሪና የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች
• 5,880 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ የመኪና ማቆሚያዎች
• 150 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች
• 13 የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች

3. የመሬት ውስጥ መሠረተ ልማት
• 17 ኪ.ሜ. የፍሳሽና የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የመጠጥ ውሃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የኤሌክትሪክ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የቴሌኮም መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የITS መስመሮች

4. የንግድ፣ የሥራ፣ የመኖሪያና የመዝናኛ ልማት
• 91 አዳዲስ የንግድ ሕንፃዎች
• 3,118 የንግድ ሱቆች አዳዲስ የተገነቡና የታደሱ
• 152 ቤቶችን የያዘ የታደሰ ሞዴል መንደር
• 33 ካፍቴሪያዎች
• 20 ሬስቶራንቶች
• 440 የታደሱ ሕንፃዎች
• 2 ቤተመጻሕፍት
• 7 የልጆች መጫወቻዎች
• 7 የስፖርት ሜዳዎችና ጂምናዚየሞች
• 7 ፏፏቴዎችና ፋውንቴኖች
• 5 የህዝብ መዝናኛና ፕላዛዎች
• ሰፊ አረንጓዴ ቦታዎች
• የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች

5. የተቋማት ልማት
– 2 የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
– 2 የፖሊስ ጣቢያ ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
– 1 የቱሪስት መረጃ ማዕከል

6. የሥራ ዕድል ፈጠራ
• በግንባታ ወቅት 23,000 ዜጎች የሥራ ዕድል አግኝተዋል።
• በቀጣይም በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ቋሚ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ፕሮጀክት ታሪካዊ አሻራቸውን ላኖሩ፣ በታለመለት ጊዜ መጠናቀቅ ሌት ተቀን ለለፉ ላስተባበሩ በየደረጃው ላሉ አመራሮች ፤ የስራ ተቋራጮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አጋራ

YouTube

አማEN