“ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዟችን በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን አለበት” – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታልን በጎበኙበት ወቅት የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ቀልጣፋና ዘመናዊ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ፣ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው ደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።
ባለ አምስት ወለሉ ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታው ሲጠናቀቅ በወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት እንደሚመራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።
የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል ነው ሲሉም አክለው አስገንዝበዋል።
